ስለ
If you cannot see special characters(ግዕዝ and عربي ) download by clicking here
አፍሪካን ሆሎኮስት (ማአፋ) የአፍሪካ ታሪክና ባህል የሚያጠና አትራፊ ያልሆነ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ የአፍሪካን ትክክለኛ፤ እውነተኛ እና የጋራ የሆነ፤ ያለፈ እና የአሁኑን የአፍሪካን ተመኩሮና ታሪክ የሚያጠና አፍሪካዊያን ምሁራንን ያሰባሰበ ማኅበር ነው፡፡ በተጨማሪ ማኅበሩ ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ለማስተማር፤ አቅምን ለመገንባት እና ሌሎችን ለማነቃቃት ስራዎችን ይቀበላል፡፡ ማኅበሩ ሁሉም ዓይነት የጫና፤ የጭፍለቃ፤ አንድን ባህል ብቻ የማንገስ ስርዓትን፤ አለመቻቻልን እና የሃይማኖታዊና የጎሳዊ ጥላቻ መገለጫዎችን አጥብቆ ያወግዛል፡፡
ተልዕኮአችን ሁሉም ሊያገኙአቸው የሚችሉ የአፍሪካን ባህልና ታሪክ የሚያሳውቁ እና አፍሪካዊ ባህል ይዘት ያላቸው ስራዎችን ማቅረብ ነው፡፡ ይህ ስራም ብዙ ባህላዊ መስተጋብሮችን እና የአፍሪካን ባህላዊ/ታሪካዊ ተመኩሮዎች ለተቀረው የዓለም ህብረተሰብ ለማቅረብ የሚያገለግል ነው፡፡ በተጨማሪም ሰባቱን ቁልፍ የአፍሪካ ህግጋት ያማከልን ነን፡፡ ጥናታችን በፍቅር ታሪክ መገለጫነት ሳይሆን ብዝሃ ህዝብን የሚያስቀድምና የሰውን ተመኩሮ የሚያዳብር ጥናት ነው፡፡ በእኛ እምነት ድንቁርና እና ጥላቻ ሊወገድ የሚችለው ከልብ የሆነ መስተጋብር እና ንግግር ሲኖር ነው፡፡ የሰብአዊነት ሂደት ውስጥም አፍሪካዊያን የራሳቸውን ልዩ የባህል ተመኩሮ ሊያበረክቱ የሚችሉት በራስ ተነሳሽነት ላይ ተመስርተው ነው፡፡
ይህ ድረ ገፅ ማንኛውንም ዓይነት ዕርዳታ አይጠይቅም፡፡ ይልቁንስ የምንጠይቀው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሚገኙትን የሚዲያ ውጤቶች እንድትገዙ ነው፡፡ ይህ ቀላል የንግድ ልውውጥ ነፃ ሚዲያ ቀጣይነት እንዲኖረውና ይህ ድረ ገፅም ይቀጥል ዘንድ ነው፡፡
GEEZ: ግዕዝ
The African Holocaust Society, inline with the African Code, recognizes Ge'ez (ግዕዝ) (script of Ethiopia) as the official Pan-African script because it is the longest surviving and only native African script still in use today. We believe an native African script is far better for writing African languages than a latin one. And thus Ge'ez needs to be integrated into the global African learning system for future expansion.
If you cannot see special characters(ግዕዝ and عربي ) download by clicking